የቢዝነስ መድረክ - አውደ-ርዕይ ፕሮግራሞች |
አውደ-ርዕይ ፕሮግራሞች (ኤግዚቢሽን) በአሁኑ ጊዜ በመላው አለም እያደገ የመጣ የንግድ እንቅስቃሴ ዘርፍ ነው፡፡ የመድረክ ትዕይንቶችና ትርኢቶች ከበለፀጉት ሀገራት ጀምሮ እስከ ታዳጊ ሀገራት አዘውትረው በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ በይዘትና በአይነቱ ልዩ ልዩ ሆኖ የሚዘጋጀው አውደ-ርዕይ የተለያዩ አለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን ለዝግጅቱ ታዳሚዎች የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነውና ከፍተኛ የንግድ ሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት አውድ ነው፡፡ የንግድ ተቋማትን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ክንዋኔዎችን ለመፈፀም መልካም አጋጣሚ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ሁኔታ በርካታ የጋርዮሽ ተግባቦትን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ አውደ-ርዕይ ዝግጅት በሁለት መልክ የሚቀርብ ሲሆን አንደኛው የተለያዩ ማህበራት የጋራ ስብስብ አድርገው የራሳቸውን የማስተዋወቅ ስራ ለማከናወን በሚያስቡበት ጊዜ ከአስተባባሪ ድርጅት ጋር የሚሰሩት ስራ ሲሆን ሁለተኛው አይነት አንድ የአውደ-ርዕይ አዘጋጅ ድርጅት በራሱ መዋቅር በአንድ የተወሰነ ጉዳይ ላይ ድርጅቶችን አሳታፊና ተሳታፊ በማድረግ የሚሰጠው ዝግጅት ነው፡፡ ታዲያ የእኛ ድርጅት ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ መስክ ይኸው ነው፡፡ አውደ-ርዕይን ለመምራት በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ የተደራጁ ማህበራትን ፕሮግራም የማስተባበር ሚና መጫወትና ድርጅታችን ራሱ በመረጠው ትይንት ላይ የተለያዩ ድርጅቶችን በመጋበዝ ዝግጅቱን ማሰናዳት ነው፡፡ ትዕንቶችን በማዘጋጀት ዙሪያ ድርጅታችን የተለያየ ስያሜ ያላቸውን የአውደ-ርዕይ ፕሮግራሞች በመንደፍ በየጊዜው አነስተኛም ይሁኑ ከፍተኛ ዝግጅቶችን ያቀርባል፡፡ በዚሁ ድህረ-ገፃችን ላይ ያዘጋጀናቸውንና የምናዘጋጃቸውን እንዲሁም በሌሎች ድርጅቶች የሚሰናዱ ፕሮግራሞችን ለጎብኝዎችና ለተሳታፊዎች ይፋ ማድረግ ነው፡፡ የመድረክና የአደባባይ ትዕይንቶችን ለተሳታፊዎች ሁሉ የምናስተዋውቅ ይሆናል፡፡ አዝናኝና አገራዊ ባዛሮች፣ ስብሰባዎች፣ የድጋፍ ጥሪዎችና ተመሳሳይ ነገሮችን እናዘጋጃለን...
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|