Text Box: Text Box:
Text Box:

 

        መፅሄት - "ሲላ" መፅሄት

 

www.liyumultimedia.com

ይህ ድህረ-ገፅ በልዩ የመረጃ ማዕከል ተሰራ

የዲዛይን ስራ - በሲሳይ መኳንንት

2011 ዓ.ም ተከፈተ


   
ድርጅታችን ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ "ሲላ" የተሰኘው መፅሄታችን ሲሆን ይህ መፅሄታችን በአማርኛ ቋንቋ በየወሩ የሚዘጋጅ በመጠኑ የአጭር አጭር ሲሆን የውስጥ ገፅ ብዛቱም 16 ነው፡፡ ይህ ባለሙሉ ቀለም መፅሄት ታትሞ በተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ አንባቢያን እጅ ይደርሳል፡፡

    እነሆ "ሲላ" ማለት ከአዕዋፋት ዝርያዎች መካከል የምትመደብ ፍጡር ስትሆን በአለም ላይ እጅግ ፈጣኗ ወፍ እንደሆነች ትታወቃለች፡፡ በእንግሊዘኛው አጠራር falcon በመባል የምትታወቀው ይህቺው ወፍ የተለያዩ መለያ ባህሪያት ቢኖሯትም እኛ ግን ለመፅሄታችን መጠሪያ ስም አድርገን የተጠቀምንባት ፍጥነቷንና ያሰበችውን ነገር ለማድረግ ትክክለኛ ውሳኔ አድርጋ በትክክል ስለምታሳካ ነውና እኛም በዚቺው ወፍ ባህሪ ላይ ተመስርተን ስራችንን እንሰራለን ለማለት ያህል ነው፡፡

    መፅሄታችን ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ላይ የሚያጠነጥኑ አጫጭር የአገር ውስጥና የውጭ አገር አነጋጋሪ ዜናዎች፣ ልዩ ልዩ እውነታዎች፣ አዳዲስ የተለቀቁ ፊልሞች፣ የሙዚቃ አልበሞችና መፅሀፍቶችን በማውጣት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡ ወቅታዊና አዳዲስ የኪነጥበብ ውጤቶችን ከየመስኩ በመሰብሰብ ወሩን ጠብቆ በሚወጣው መፅሄታችን ላይ በመግለፅ በተፈለጉ ስፍራዎች ሁሉ እናሰራጫለን፡፡

    በዚህ ረገድ አዳዲስ ስራ የሰሩ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በአካልም ሆነ በሰጠነው አድራሻ መሰረት ስራዎቻቸውን ቢልኩልን ያለክፍያ እናወጣለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በድረ-ገፃችንም ላይ በተመደበላቸው ስፍራ ላይ ምስላቸውን እንለቃለን፡፡ የእኛ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከስፖንሰሮችና ማስታወቂያ ከሚጠቀሙ ድርጅቶች ይሆናል፡፡

    በመሆኑም የማስታወቂያ ሽፋን ማግኘት የሚፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ካሉ ባለን የማስታወቂያ ተምን መሰረት አስፈላጊውን ክፍያ ለሚፈፅሙ ሁሉ በጥያቄአቸው መሰረት እናስተናግዳለን፡፡ በዚህ መፅሄት ላይ ምርትና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ የሚፈልጉ አከላትን በታላቅ በደስታ እንቀበላለን፡፡

    በመፅሄታችንና በሬድዮ ፕሮግራማችን ላይ ስፖንሰር ለሚያደርጉን አካላት እና ማስታወቂያ ለሚያሰሩ ድርጅቶች በቅናሽ ዋጋ በድረ-ገፃችንም ላይ የማስታወቂያ ሽፋን እንደምንሰጣቸው ቃል እንገባለን፡፡ 

 

 

 

Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools.

Text Box: መግቢያ
Text Box: ስለእኛ
Text Box: አድራሻ
Text Box: መነሻ ገፅ
Text Box: የሬድዮ  ፕሮግራም
Text Box: የማስታወቂያ  ስራ
Text Box: የግንኙነት  ስራ
Text Box: የቢዝነስ  መድረክ
Text Box: የድጂታል  ስራ
Text Box: የመፅሀፍ  ግምገማ
Text Box: መፅሄት
Text Box: ሽልማት
Text Box: ቤተ-መዘክር
Text Box: Text Box: አዳዲስ  መፅሀፍት
Text Box: አዳዲስ  ፊልሞች
Text Box: አዳዲስ  ሙዚቃዎች
Warnemuende, daily newspapers and magazines in a newspaper stand Stock  Photo - AlamyText Box: Text Box: