Text Box: Text Box:
Text Box:

 

        የግንኙነት  ስራ

 

www.liyumultimedia.com

ይህ ድህረ-ገፅ በልዩ የመረጃ ማዕከል ተሰራ

የዲዛይን ስራ - በሲሳይ መኳንንት

2011 ዓ.ም ተከፈተ

 
   
እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ አብዛኛው ስራ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ የሚከናወን አይደለም፡፡ አንድን ውጥን ሀሳብ ለማከናወን ብዙ ትግልና ውጣ ውረድ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር ከሌላው አለም ጋር ስንተያይ ወደኋላ አስቀርቶናል፡፡ በቀላሉ ልንሰራው የምንችለው ነገር ብዙ ጊዜ ሲፈጅብን ይስተዋላል፡፡

    ይህ ችግር እንደሀገር ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ህይወት ሳይቀር ከፍተኛ መስዋዕት እንድንከፍል ዳርጎናል፡፡ ትናንት ሰርተነው ልናልፈው የሚገባንን ነገር ለዛሬና ለነገ ሲከርም እናየዋለን፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ የሚጠፋው ጊዜና ገንዘብ ቀላል አይደለም፡፡ በርካታ ባለሙያዎችም ውጥናቸው በመዘግየቱና ፍፃሜ ሳያገኝ በመቅረቱ ባክነውና ተቸግረው ይቀራሉ፡፡

    ይህንን ክፍተት ለማጥበብና ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረግ ብዙም የተለየ ሙከራ ሲከናወን አናይም፡፡ የሰው ሀይል ብክነትን ለመቀነስ አንድ ራሱን የቻለ ትልቅ መዋቅራዊ አሰራር ለመፍጠር በመንግስትም ሆነ በግል ድርጅቶች ሊሰራ ሲገባ የሰራተኛና አሰሪ ወኪል ድርጅቶችን እንደዋዛ ከማየት በስተቀር በየጊዜው ለሚፈጠረው የስራ እጦት ብቻ ሳይሆን የክህሎት ጥበቃ ላይ በሚደረግ ቁጥጥር ላይ ይመለከተኛል የሚል አካል በመጥፋቱ የተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለችግር ተጋላጭ እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡

    በፈጠራ ሰዎችና በኪነጥበብ ባለሙያዎች ላይ የሚስተዋለውን ፈተና በርካቶች ቢረዱትም አዳዲስ ተስፈኛ ወጣቶችን ብቻ ሳይሆን ጥሩ ልምድና ብቃት ያላቸው ሰዎች ሳይቀሩ ልፋታቸው መና ሲቀር አዛኞች ብቻ ሆነን ከመገኘት ባለፈ ክህሎታቸውን በአግባቡ መጠቀም የሚችሉበትን መፍትሄ ስንዘረጋላቸው አንታይም፡፡ በውጭው አለም "idea incubation" የሚባለው ነገር በእኛ አገር የተለመደ ባለመሆኑ ድንቅ ሀሳብ ያላቸው ዜጎች እንዲሁ እንደባከኑና እንደባዘኑ ቀርተዋል፡፡

    ታዲያ ይህንን ጉድለት ለማስተካከልና በመጠኑም ቢሆን ለማሻሻል በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በስነፅህፍና በዕደጥበብ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሙያ መደጋገፍ እንዲያደርጉ አንዱ መሰራት የሚያስፈልገው ጉዳይ በመሆኑ በዘርፉ ላይ መዋዕለ-ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ግለሰቦችም ትንሽ በር ቢከፍት ብለን ድርጅታችን ፈላጊና ተፈላጊን በማገናኘት ላይ የራሱን ሚና ለመወጣት ያስባል፡፡ መድረኮችን ለማመቻቸት አንድ ጣቢያ መክፈቱን ስለምናምን በሙያው ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የሀሳብና የአድራሻ ልውውጥ እንዲያደርጉ እንወዳለን፡፡ ለዚህም ፍቃደኛ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ የሚገናኙበትን መስመር በመዘርጋት የጋራ ትብብር እንዲያከናውኑ እናስችላቸዋለን፡፡

    ይህንን አሰራር ቀላል ለማድረግ ያህል ከዚህ ዌብሳይት በተጨማሪ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል የሞባይል መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) በቅርቡ ለህዝብ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ መተግበሪያውን የሚጠቀም ማንኛውም ግለሰብ በሙዚቃ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በፊልም፣ በዕደ-ጥበብ፣ በቴክኖሎጂ እና በተለያዩ የመድረክና የፋሽን ስራዎች ላይ ተሰጥኦ አለኝ የሚል ሁሉ በቀላሉ መጠቀም እንዲችል ያደርገዋል፡፡

    የግንኙነቱን ስራ በምናከናውንበት ጊዜ ነፃ አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን በሌላ በኩል እንደሁኔታው መጠነኛ ክፍያ የምንጠይቅባቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ የጋራ ትብብር ውስጥ በጎ ፍቃደኛ ባለሙያዎችና ጀማሪ ባለተሰጥኦዎች የሙያ ድርሻቸውንና የስልክ ቁጥራቸውን በመግለፅ ቀና ትብብር እንዲያደርጉና ፍላጎታቸውን እንዲገልፁልን እንሻለን፡፡ በድረ-ገፃችን ላይ የድርጅታቸውን ወይም የግል ስማቸውን፣ የሙያ ድርሻቸውንና አድራሻቸውን እንደየፍላጎታቸው እንገልፃለን፡፡

    ይህም ብቻ ሳይሆን ባለሙያዎቹ ለሚገጥማቸው አገራዊ ችግር መፍትሄ እንዲዘረጉ ከሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናትና የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የጋራ ውይይት እንዲያደርጉ የተለያየ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማሰባሰብ ረገድ ባለሙያዎቹ በስራቸውና በህይወታቸው ላይ ለሚጋረጡባቸው አደጋዎችና ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ መንገድ እናመቻቻለን፡፡

 

 

 

Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools.

Text Box: መግቢያ
Text Box: ስለእኛ
Text Box: አድራሻ
Text Box: መነሻ ገፅ
Text Box: የሬድዮ  ፕሮግራም
Text Box: የማስታወቂያ  ስራ
Text Box: የግንኙነት  ስራ
Text Box: የቢዝነስ  መድረክ
Text Box: የድጂታል  ስራ
Text Box: የመፅሀፍ  ግምገማ
Text Box: መፅሄት
Text Box: ሽልማት
Text Box: ቤተ-መዘክር
Text Box: Text Box: የሙዚቃ  ባለሙያዎች
Text Box: የስነ-ፅሁፍ  ባለሙያዎች
Text Box: የፊልም  ባለሙያዎች
Text Box: የዕደ-ጥበብ  ባለሙያዎች
Text Box: Text Box: