የድጂታል ስራ |
የዲጅታሉ አለም ፈጣንና የሰው ሀይል ቆጣቢ ነው፡፡ በዚያ ላይ በየትኛውም አለም ለማንኛውም ሰው በቀላሉ ይደርሳል፡፡ የገንዘብ ወጭንም ይቆጥባል፡፡ የጎን ጉዳት ቢኖረውም በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሚዛናዊነትና ተአማኒነት ቢጎድለውም አለምን በቀላሉ ያቀራርባል፡፡ ስራን ያቀላጥፋል፡፡ ያቃልላል፡፡
የድህረ-ገፅ ስራዎች፡- ድርጅታችን ከዚህ ቀደም የሰራቸውና ሊሰራቸውም የሚችላቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይኖራሉ፡፡ በድህረ-ገፅ ስራ ለተለያዩ ድርጅቶችና ዕውቅ ግለሰቦች አስፈላጊውን ሙያዊ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በይበልጥ በዲዛይን ስራው ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን እንደየአስፈላጊነቱ ተጨማሪ እገዛዎችንም በማቅረብ የተቀላጠፈ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አስፈላጊ መረጃዎችን ከደምበኞች በመቀበል በተፈለገው መንገድ ሰርቶ ያስረክባል... ይመልከቱ
የሞባይል አፕሊኬሽን ስራዎች፡- የሞባይል አፕሊኬሽን ስራዎች በብዙ መልኩ ተመራጭ እየሆኑ በመጡበት በዚህ ጊዜ ድርጅታችን በያዘው ዕቅድ መሰረት በሶስት አይነት አሰራር አፕሊኬሽኖችን ለተጠቃሚዎችና ለተገልጋዮች ያደርሳል፡፡ አንደኛ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ድርጅታችን ራሱ አምርቶ ያቀርባል፡፡ ሁለተኛ የፈጠራ ውጤቶችን ከተለያዩ የፈጠራ ሰዎች ይገዛል፡፡ ሶስተኛ አፕሊኬሽን እንዲሰራላቸው የሚፈልጉ አካላት በሚኖሩበት ጊዜ በጥያቄአቸው መሰረት ከፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር የተፈለገውን ስራ ሰርቶ ያስረክባል... ይመልከቱ
የግራፊክስ ስራ፡- በዲጅታል ስራዎች ውስጥ ከምንሰራቸው ስራዎች መካከል የግራፊክስ ስራ አንዱ ነው፡፡ ለተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅቶች የሚያማምሩና ትክክለኛ መልዕክት ሊያደርሱ የሚችሉ የግራፊክስ ስራዎችን ይሰራል፡፡ ለአውደ-ርዕይ፣ ለኮንሰርቶች፣ ለስብሰባ ዝግጅቶች፣ ለሰርግ ወረቀት፣ ለምርቃት፣ ለቢዝነስ ካርድና ለመሳሰሉት ነገሮች ውብ የግራፊክስ ስራዎችን እንሰራለን... ይመልከቱ
አዳዲስ ምርቶቻችንን በዚሁ ድረ-ገፃችን (ዌብሳይታችን) ላይ የምንገለፅ ሲሆን ጥቅል ግዥ ለሚፈልጉም ሆነ በተናጠል ሽያጭ እናከናውናለን፡፡ በተጨማሪም ሻጭና ገዥዎችን በማገናኘት የገበያ ድርድር እናደርጋለን፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር በሌሎች አገሮች ላይ የተለመደ ቢሆንም አገራችን ኢትዮጵያም ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝና አለም የደረሰበት ደረጃ ላይ እንድትደርስ ድርጅታችን የበኩልን ድርሻ ይወጣል፡፡ የፈጠራ ሰዎች የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙም የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን አዲስ ግኝት ላመጡና በርካቶችን ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ስራ ለሰሩ ሰዎች በየአመቱ በሚኖረው "አላማ ሽልማት" በተሰኘው ስነ-ስርአት ላይ በፈጠራ ስራ ራሱን የቻለ ሽልማት እንሰጣለን፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ባለቤት ማረጋገጫ የተሰጣቸውን ግለሰቦች ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የምናገናኝ ሲሆን የትም ቦታ ያልታዩ አዳዲስ ስራዎችንም ከባለሙያዎች ጋር በመነጋገር መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ሲኖሩ የምክር አገልግሎት በመስጠት እገዛ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ እናመቻቻለን፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን እናበረታታለን፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|