የሬድዮ ፕሮግራም - "ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም |
ሰናይ ዓለም የተሰኘው የሬድዮ ፕሮግራማችን በሳምንት ሶስት ጊዜ በጥቅሉ ለሶስት ሰአታት ያህል በ ሬድዮ ጣቢያ በዕለተ፣ እና- ከ እስከ- ሰዓት የሚተላለፍ ሲሆን በሶስት ዋና ዋና መሰናዶዎች ለአድማጮች ይቀርባል፡፡ በፍቅር በምንሰራው በዚህ የሬድዮ ፕሮግራማችን ላይ መላ ኢትዮጵያውያንን ያማከለ ሰናይ ተግባራትን በመዳሰስ አዝናኝ በሆነ መልኩ ይቀርባል፡፡ በአለም አቀፍ ዙሪያ የሚከናወኑ መልካምና በጎ ታሪኮችን በመቃኘት ወገኖቻችንን ምርታማ ዜጋ ለማድረግ እንተጋለን፡፡ በስነ-ምግባር የታነፀ አስተዋይ ትውልድ እንዲኖር የምንጊዜም ምኞታችን በመሆኑ ፕሮግራሙን በተቀላጠፈና ዘና በሚያደርግ ሁኔታ እናቀርባለን፡፡ የፕሮግራሞቹ ይዘት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
መልካም ታሪከ ዜናዎች፡- የተሰኘው ይህ አንደኛው መሰናዶ የሚያተኩረው በአለም ዙሪያ ላይ የተከናወኑ መልካምና በጎ ተግባራትን በመዳሰስ አጫጫር ታሪኮችን ለአድማጮች ማቅረብ ይሆናል፡፡ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና በኢንተርኔቱ አለም የተሰራጩ መረጃዎች ማራኪ በሆነ አቀራረብ ለአድማጮች ይደርሳሉ፡፡ ሰዎችን ለሰናይ ተግባራት ማነሳሳት የሚችሉ ድንቃ ድንቅ ዜናዎች ባጭር ባጭሩ ይቀርባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የተከናወኑ መልካም ተግባራትና ሊደረጉ የታቀዱ ዝግጅቶች ካሉ መረጃዎቹ ለህብረተሰቡ የሚተላለፉበት ፕሮግራም ይሆናል... ዝርዝር
ሰናይ እንግዳ፡- የተሰኘው ፕሮግራም ሁለተኛው መሰናዶ ሲሆን ከተጋባዥ እንግዳ ጋር የአንድ ለአንድ ቃለመጠይቅ የሚቀርብበት ፕሮግራም ይሆናል፡፡ በመሆኑም ሰዎች የግል ታሪካቸውን፣ የስራ ተሞክሯቸውንና ስለዚህች አለም ያላቸውን ምልከታና ዕይታ አዝናኝና አስተማሪ በሆነ መልኩ የሚገልፁበት የአየር ሰዓት ነው፡፡ እንግዶቻችን በማንኛውም የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ፣ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና የተለያየ እምነት ያላቸው ቢሆኑም ጠቃሚ ሀሳባቸውንና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት የሬድዮ መድረክ ይሆናል... ዝርዝር
የመፍትሄ ሀሳብ፡- በተሰኘው በዚህ ሶስተኛው የፕሮግራም አይነት ላይ ከሬድዮ ፕሮግራማችን አድማጮች ጋር በሚደረግ የስልክ ውይይት የፕሮግራሙ አቅራቢዎች ለሚያነሱት ወቅታዊ አገራዊ ጥያቄ አድማጮች ሀሳባቸውን ለህብረተሰቡ የሚያጋሩበትና በተጨማሪም የተለየ የቀድሞ ልምዳቸውን በማጋራት ማህበረሰባችን እንዲማማር የጋራ የውይይት መድረክ መፍጠር ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ አወዛጋቢ ሆነው ህዝቡን ግራ የሚያጋቡ ነገሮች መፍትሄ የሚያገኙበትና ለማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከራሱ ከህዝቡ በሚደረግ ጥቆማ እልባት እንዲሰጣቸው ለማድረግ ታልሞ አየር ላይ የሚውል ዝግጅት ነው፡፡ ሁነኛ ሀሳባዊ ሰዎችም የመናገር ዕድል እንዲያገኙ ማስቻልና አገራችን ከራሷ ዜጎች አዳዲስ ዕይታዎችን እንድታገኝ ማስቻል ነው፡፡ መልካምና ጠቃሚ ሀሳብ እያላቸው ጥሩ አጋጣሚ በማጣታቸው የተነሳ ህዝቡ ያላወቃቸውን ግለሰቦች ለመተዋወቅም መንገድ ይፈጥራል... ዝርዝር እነሆ ይህንን የሬድዮ ፕሮግራም ስፖንሰር ሊያደርጉ የሚችሉ ድርጅቶችን በታላቅ አክብሮት ስንቀበል በፕሮግራሙ ላይ አገልግሎታችሁንና ምርታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ አካላት አጋር እንድትሆኑን ስንጠይቅ በትህትና ነው፡፡ በሬድዮ ፕሮግራማችንና በመፅሄታችን ላይ ስፖንሰር ለሚያደርጉን አካላት እና ማስታወቂያ ለሚያሰሩ ድርጅቶች በቅናሽ ዋጋ በድረ-ገፃችንም ላይ የማስታወቂያ ሽፋን እንደምንሰጣቸው ቃል እንገባለን፡፡ ከዚህ ባሻገር የተከበራችሁ ውድ አድማጮች በፕሮግራማችን ላይ አስተያየታችሁንና ድጋፋችሁን እንድትገልፁልን እንጠይቃለን፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|