Text Box: Text Box:
Text Box:

 

        የማስታወቂያ  ስራ

 

www.liyumultimedia.com

ይህ ድህረ-ገፅ በልዩ የመረጃ ማዕከል ተሰራ

የዲዛይን ስራ - በሲሳይ መኳንንት

2011 ዓ.ም ተከፈተ

 
   
እንደሚታወቀው የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በመላው አለም ዙሪያ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም የዲጅታል ቴክኖሎጂ ከመጣ ወዲህ ጀምሮ በዚህ ዘርፍ ላይ የሚደረገው የገበያ ፉክክር ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ምርትንና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ ሲባል ድርጅቶችና ተቋማት ከፍተኛ የገንዘብ ወጭ ያደርጋሉ፡፡

    ነባር ድርጅቶችም ሆኑ አዳዲስ መጤ ድርጅቶች ከገበያ ፉክክር ላለመውጣት የተለያየ ቴክኒክ ቢዘረጉም ያለማስታወቂያ ግን መንገዳቸው ቀላል አይደለም፡፡ የገበያ ፍላጎት ባለበት አካባቢ በተጠቃሚው ዘንድ ለመታወቅ ይብዛም ይነስም የማስታወቂያ ዘዴ መጠቀሙ መልካም ነው፡፡ የማስታወቂያ አይነቶቹ ልዩ ልዩ ሲሆኑ የእኛ ድርጅት በይበልጥ በሚከተሉት የብዙሀን መገናኛ አይነቶች ማስታወቂያዎችን የመስራት ተልዕኮ አለው፡፡  

 

የቴሌቭዥን ማስታወቂያ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ መንፈሳዊ ጣቢያዎችን ሳይጨምር በናይል ሳት የሚተላለፉና በአለም አቀፍ ዙሪያ የሚሰራጩ የመንግስትና የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በቁጥር ከሃያ በላይ ደርሰዋል፡፡ የግል ጣቢያዎችም ሆኑ መንግስት የሚደጉማቸውን ህዝባዊ ጣቢያዎች ጨምሮ ዋና የገቢ ምንጫቸው በማስታወቂያ በኩል የሚያገኙት ገንዘብ ነው፡፡ ለነዚህ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ደግሞ ግብአት አቀባይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ከነዚያም ውስጥ የእኛ ድርጅት አንዱ ሲሆን በቴሌቭዥን ማስታወቂያ የተለያዩ ክፍያዎችን በማውጣት የምርት ስራዎችን ይሰራል... ዝርዝር

 

የሬድዮ ማስታወቂያ፡- በሬድዮ ስርጭት አገልግሎት ላይ ተመስርተው የተቋቋሙ ድርጅቶች በብሮድካስቲንግ ሚዲያው ሌላ አማራጭ የማስታወቂያ ማስተላለፊያ ተቋሞች ናቸው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ በይበልጥ የሚደመጡ በአለም አቀፍ፣ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች በረጅምና በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ የድምፅ አስተላላፊ ብዙሀን መገናኛ መስመሮች በጥቅሉ ሲደመሩ ከሃያ በላይ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚሁ ድርጅቶችም በመንግስት፣ በልዩ ልዩ ተቋማትና በተለያዩ ባለሀብቶች አማካኝነት ቢከፈቱም ዋና መተዳደሪያ ገቢአቸው ማስታወቂያ ነውና ለነዚህ ጣቢያዎችም የተለያዩ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሰርቶ ያቀርባል... ዝርዝር

   

የህትመት ማስታወቂያ፡- እንደዛሬው ዘመን ፈጣን የማስታወቂያ ማስተላለፊያ መንገዶች ባልዳበሩበት ዘመን የህትመት ዘርፉ ለረጅም አመታት በአለማችን ላይ ግልጋሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ድረስ ቢሆን ጥቅም እየሰጠ ይገኛል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም የጋዜጣና መፅሄት ስርጭት አሁንም ድረስ ያልተቀቋረጠ በመሆኑ ለማስታወቂያ ሌላኛው አማራጭ መገልገያ መሳሪያ ነውና በህትመት ላይ ማስታወቂያ እንዲተላለፍላቸው ለሚፈልጉ ድርጅቶችም የተለያየ የዋጋ ተመን ስላለን አገልግሎት እንሰጣለን... ዝርዝር

 

የኢንተርኔት ማስታወቂያ፡- ይህ የማስታወቂያ ዘርፍ ባደጉት ሀገራት ዘንድ በስፋት እየተጠቀሙበት የሚገኝ ሲሆን በእኛም አገር ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ መንግስታዊና የግል ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦችን ጨምሮ የራሳቸውን ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት አይነተኛ የማስታወቂያ ዘርፍ ነው፡፡ በመላው አለም ዙሪያ ለሃያ አራት ሰአት ያህል ማንኛውም የበይነ-መረብ ማለትም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሊገለገልበት የሚችል የማስታወቂያ አይነት ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ ድረ-ገፆች ላይ በቀላሉ ሊታይ የሚችል የማስታወቂያ ዘርፍ በመሆኑ የእኛም ድርጅት በቀጣይነት የተለያዩ ንድፎችን በመስራት የኦንላይን ግብይት በሀገራችን እስኪጀመር ድረስ በአካል ግብይት በማከናወን አገልግሎት እንሰጣለን... ዝርዝር

 

 

 

Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools.

Text Box: መግቢያ
Text Box: ስለእኛ
Text Box: አድራሻ
Text Box: መነሻ ገፅ
Text Box: የሬድዮ  ፕሮግራም
Text Box: የማስታወቂያ  ስራ
Text Box: የግንኙነት  ስራ
Text Box: የቢዝነስ  መድረክ
Text Box: የድጂታል  ስራ
Text Box: የመፅሀፍ  ግምገማ
Text Box: መፅሄት
Text Box: ሽልማት
Text Box: ቤተ-መዘክር
Text Box: Text Box: የቴሌቭዥን
Text Box: የጋዜጣ
Text Box: የሬድዮ
Text Box: የኢንተርኔት
Text Box: Text Box: