ስለእኛ |
1. "ሰናይ አለም" የተሰኘ የሬድዮ ፕሮግራም ማዘጋጀት 2. በህትመት፣ በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያና በኢንተርኔት ማስታወቂያዎች ላይ መስራት 3. የግንኙነትና የፕሮሞሽን ስራዎችን ማከናወን 4. የሙዚቃ ግጥምና ዜማ መድረስና ቪድዮ ማቀናበር 5. የተለያዩ የመድረክና አውደ-ርዕይ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት 6. የድህረ-ገፅ፣ የሞባይል አፕሊኬሽኖችንና የግራፊክስ ስራዎችን መስራት 7. የንግድ ንድፈ ሀሳብ (ቢዝነስ ፕሮፖዛል) ማዘጋጀት 8. የመፅሀፍ የአርትኦትና እርማት ስራ መስራት 9. የህብረት አገር ጉብኝት ማሰናዳትና ማመቻቸት 10. "ሲላ" የተሰኘች የኪነጥበብ መረጃ ሰጭ አጭር መፅሄት ማዘጋጀት 11. "አላማ" የተሰኘ አምስት አይነት ሽልማት በየአመቱ ማቅረብ 12. "ሀበሻ ቤተ-መዘክር" በሚል የዝነኛ ኢትዮጵያውያንን ፎቶ ያሰባሰበ የግል አነስተኛ ሙዚየም ቤት (ክፍል) መክፈት ናቸው፡፡
በነዚህና ተዛማጅ በሆኑ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የምንሰራ ሲሆን ብቃት ባላቸው ሰራተኞቻችን በመታገዝ የድርጅታችንን አላማና ራዕይ በትጋት እንከውናለን፡፡ አገራችንን ማለትም ዜጎቻችንን ምንጊዜም አቅማችን በፈቀደ ልክ በቀና መንፈስ ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል፡፡ ከስራ አጋርና ደምበኞቻችንን ጋር በመተባበር የዜግነትና የሙያ ግዴታችንን ለመፈፀም ፅኑ ፍላጎት አለን፡፡ በእያንዳንዱ የስራ አይነት ዝርዝር መረጃዎች ማግኘት ለሚፈልጉ አካላት ሁሉ በየሰበዙ (ሊንኩ) ላይ ለማብራራት ስለሞከርን እንዲመለከቱት እንጋብዛለን፡፡ ይህንን ድረ-ገፃችንን ገንብተን የሰራነውም በማንኛውም ሁኔታና ሰዓት ከእኛ ጋር አብረው ሊሰሩ ለሚወዱ ሁሉ ግልፅ መረጃ ለመስጠት ያህል ነውና በምንግባባበት የአማርኛ ቋንቋ በጥንቃቄ አስፍረናል፡፡ በቋንቋ ችግር ምክንያት መግባባት ለተቸገሩ ወይንም ኮምፒውተራቸው አማርኛ ማንበብ ለማይችል ተገልጋዮች ጥያቄዎቻቸውን በእንግሊዘኛ ፅፈው በመልዕክት መቀበያ አድራሻዎቻችን ቢልኩልን ምላሽ እንሰጣለን፡፡ እንግዲህ ይህንን በመረዳት እኛም ለሌሎች፣ ሌላውም ለእኛ የቅብብሎሽ ስራ እንሰራለን ብለን እናምናለን፡፡ ምናልባት ድክመት ቢታይብን ተገልጋዮቻችን ሀሳብና ስሜታቸውን በቅን መንፈስ ቢገልፁልን ለመታረም ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ የአምላክ ፈቃድ ሆኖ ጅማሬአችን መልካም ከሆነ የተሻለ ዘላቂ ስራ በመስራት ወደፊትም ቢሆን አድማሳችንን በማስፋት የተለያዩ ነገሮችን በማካተት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንፈልጋለን፡፡ ህልማችን ረጅም፣ ምኞታችን ብዙ ነው፡፡ አለም የደረሰበት ደረጃ ላይ ብቻ ሳይሆን ከእኛ ተርፎ ወደ ሌላው አለም የሚሻገር ስራ መስራትም እንፈልጋለን፡፡ ይህም እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይሳካልናል ብለን እናምናለን፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|