ሽልማት - "አላማ " ሽልማት |
ምንም እንኳ የምናበረክተው ነገር በቁሳዊ ወይም በገንዘብ ሲለካ አነስተኛ መስሎ ቢታይም ከሽልማቱ ባሻገር ግን ተሸላሚዎቹ አካላት ለሰሩት ስራ ህዝባቸው ወይም አገራቸው ክብር እንደሰጠቻቸው ማሳያ እንደሆነ እንዲረዱት ያህል ሲሆን ይህንንም ሀሳብ ሰዎች በቀላሉ ይረዱታል ብለን እናስባለን፡፡ በተለይም ለአሁኑ ትውልድ አንድ ማበረታቻ ነገር ሆኖት ህዝቡንና አገሩን ለማገልገል ቀና ሀሳብ ይዞ እንዲነሳ ይረዳዋል የሚል እምነት አለን፡፡ ሰዎች በተፈጥሯቸው ለሰሩት ስራ ዋጋና ክብር ሲሰጣቸው ለተሻለ ስራ እንደሚነሳሱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ድካምና ልፈታቸውን የሚረዳላቸው አካል እንዳለ ከተረዱ ይበልጥ በርትተው ይሰራሉ፡፡ የጥረት መንፈስ በውስጣቸው የሞላ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው በርካቶችን ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ነገር የመስራት ዝንባሌ አላቸውና ጥረትና ሙከራቸውን ሌላው አካል ተረድቶ ድጋፍ ቢያደርግላቸው ደግሞ ሁሌም በትጋት እንዲሰሩ ያግዛቸዋል፡፡ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ አገር ውስጥ እየኖርን በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው አገራቸውን የሚያገለግሉ ዜጎችን ለተሻለ ስራ አለማበረታታት አግባብ አይሆንም፡፡ የተለያዩ አገራት ከዜጎቻቸው አልፈው ሌሎች የውጨጭ ተወላጅ ሰዎችንም በሽልማት ይደግፋሉ፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ በየአካባቢው ያሉትን ወገኖቻችንን የስራ ውጤታቸውን በማየት ራሱን የቻለ ገፀ-በረከት ብንሰጣቸው ነፃ ስጦታ ሳይሆን ላደረጉልን የዜግነት ድርሻ ምላሽ የሚሆን ነገር እንደሰጠናቸው ይቆጠራል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም እኛም ለጅማሬ ያህል በአምስት ዘርፎች ማለትም በፈጠራ ስራ፣ በበጎ አድራጎት፣ ታታሪ ሴት፣ ተስፈኛ ወጣትና ልዩ ተሸላሚ በመምረጥ አንድ ብለን ለመጀመር አስበናል፡፡ እጩዎችን ለመውሰድ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን በሚያሰራጯቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሰን የምንወስድ ሲሆን የሚዲያ ሽፋን ያላገኙትንም በግለሰቦችና በተለያዩ ተቋማት ጥቆማ መሰረት የራሳችንን የማጣራት ስራ ሰርተን ተሸላሚዎችን እርመርጣለን፡፡ ሽልማቱ የተበረከተላቸውን አካላት ታሪክ በዚሁ ድረ-ገፃችን ላይ የምናቀርብ ሲሆን ከዚያም ባለፈ በሬድዮ ፕሮግራማችን ላይ በቃለ-መጠይቅ መልክ ለአድማጮች እናቀርባቸዋለን፡፡ ይህንን የሽልማት ስነ-ስርአት በገንዘብና በሀሳብ የሚደግፉንን ድርጅቶችና ግለሰቦች የምንፈልግ ሲሆን አቅማችን እየተጠናከረ በሚሄድበት ጊዜ በበርካታ ዘርፎች ዜጎቻችንን መሸለም እንፈልጋለን፡፡ በሀገራችን የሽልማት ተቋማት እንዲበራከቱ ልባዊ መሻታችን ሲሆን ከህፃናት እስከ እስከ አዛውንቶች ድረስ የሚዘልቅ ልዩ ልዩ ሸላሚ ድርጅት ኖሮ ብናይ ደስታችን ወደር የለውም፡፡ አላማቸውን ተረድተን በ"አላማ" ብንሸልማቸው ለእኛ ደስታና ኩታችን ነው፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|