Text Box: Text Box:
Text Box:

 

        ቤተ-መዘክር - "ሀበሻ " ቤተ-መዘክር

 

www.liyumultimedia.com

ይህ ድህረ-ገፅ በልዩ የመረጃ ማዕከል ተሰራ

የዲዛይን ስራ - በሲሳይ መኳንንት

2011 ዓ.ም ተከፈተ


    
"ሀበሻ ቤተ-መዘክር" በሚል በአይነቱ በአገራችን አዲስ የሆነ የግል ሙዚየም ለመክፈት ስናስብ የሀገራችን መንግስት ለዚህ አይነቱ ጥያቄ ምን አይነት ምላሽ ሊሰጠን እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር ባይኖርም ይህ በእቅድ የተያዘ ጉዳይ በመሆኑ ፍቃድ አግኝተን የከፈትነው ተቋም አለመሆኑን ከወዲሁ መግለፅ እንወዳለን፡፡

    እንዲያም ቢሆን ግን በሌላው አለም እንደሚደረገው ሁሉ እኛም በጣም አነስተኛ በሆነ ቤት ውስጥ የሀገራችንን ባለውለታዎች ማስታወስ ስለምንፈልግ መረጃዎች በማሰባሰብ መታሰቢያ የመገንባት አላማ አለን፡፡ ልክ እንደ አክሱምና ላሊበላ ወይም ሌሎች ቁሳዊና ተጨባጭ ያልሆኑ ቅርሶቻችን ሁሉ ቀደምት ዜጎቻችንም ለሀገራቸው የተለያየ አስዋፅኦ አበርክተው ነገር ግን ትውልድ በየጊዜው ሊዘክራቸው ሲገባ የተረሱትን ወገኖቻችንን በአንድ ጣራ ስር ፎቶአቸውን በማሰባሰብ አሁን ላለው ትውልድ ማሳያ ማዕከል የመክፈት እቅድ አለን፡፡

    ከዚህ ቀደም በበይነ መረብ ማለትም በኢንተርኔት ላይ የሰራናቸውን የግል ስራዎቻችንን በአንድ ቤት ውስጥ ፎቷቸውን በማሰባሰብ የራሳችንን ስራ ለህዝብ ይፋ ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ የተበታተኑ መረጃዎችን በበጎ ፈቃድ በመስጠት ላሰብነው ስራ ትብብር የሚያደርጉልን ወገኖች ማግኘት እንሻለን፡፡

    ለዛሬዋ ኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ መድረስ በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕት ከፍለዋል፡፡ የእነዚያን ሰዎች ማንነትና ስራ ለህዝብና ለትውልድ የማስተላለፍ ሀላፊነት አለብን፡፡ በመሆኑም ቅን በሆነ መንገድና ሚዛዊነት በተሞላበት መንፈስ ግለሰቦቹን በማስታወስ በየጊዜው መረጃዎችን በማደስና በማጠናቀር ሰፊ መዘከሪያ ቦታ የመገንባት አላማ አለን፡፡

    መጥፎ ልማድና ባህል ሆኖብን ለሰው በተለይ ለዜጎቻችን ዋጋ የመንፈግ ችግር አለብን፡፡ ሰው ከሞተ በኋላ ከንቱ ውዳሴና ሙገሳ ከማቅረብ ውጭ በህይወት እያለም ሆነ አንዴ ከሞተ በኋላ ግለሰቡን በማስታወስ ደካማና ጠንካራ ጎኑን ከነስራው ጭምር ለመዘከር ያለን ተነሳሽነት አነስተኛ ነው፡፡ የገዛ ወገኖቻችንን ከማድነቅና ከማመስገን ይልቅ በሚገባ ለማናውቃቸው የውጭ ዜጎች አድናቆት ከፍ ያለ ነው፡፡

    ኢትዮጵያ ዛሬ የተገነባች አገር አይደለችም፡፡ ከሮማም ትቀድማለች፡፡ እኛው በገዛ ድክመታችን መረጃዎቻችንን አጠናክረን ባለመያዛችን የተቀረው አለም ስለኢትዮጵያውያን ማወቅ አልቻለም፡፡ ጎብኚዎች አገራችንን ሲጎበኙ የምናሳየው ነገር ሀውልቶቻችንን ነው፡፡ ከሀውልቶቻችን በስተጀርባ ግን በርካታ ቀራፂና ግንበኞች ነበሩን፡፡

    ለቤተ-መዘክሩ ስራ ከወዲሁ ናሙና ለማሳየት ያህል ከዚህ ቀደም በድረ-ገፃችን የተሰሩትን ምስሎች በጥቂቱ ከዚህ በታች አቅርበናል፡፡

 

 

 

Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools.

Text Box: መግቢያ
Text Box: ስለእኛ
Text Box: አድራሻ
Text Box: መነሻ ገፅ
Text Box: የሬድዮ  ፕሮግራም
Text Box: የማስታወቂያ  ስራ
Text Box: የግንኙነት  ስራ
Text Box: የቢዝነስ  መድረክ
Text Box: የድጂታል  ስራ
Text Box: የመፅሀፍ  ግምገማ
Text Box: መፅሄት
Text Box: ሽልማት
Text Box: ቤተ-መዘክር
Text Box: Text Box: