የማስታወቂያ ስራ - የሬድዮ |
የሬድዮ ማስታወቂያ፡- በሬድዮ ስርጭት አገልግሎት ላይ ተመስርተው የተቋቋሙ ድርጅቶች በብሮድካስቲንግ ሚዲያው ሌላ አማራጭ የማስታወቂያ ማስተላለፊያ ተቋሞች ናቸው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ በይበልጥ የሚደመጡ በአለም አቀፍ፣ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች በረጅምና በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ የድምፅ አስተላላፊ ብዙሀን መገናኛ መስመሮች በጥቅሉ ሲደመሩ ከሃያ በላይ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚሁ ድርጅቶችም በመንግስት፣ በልዩ ልዩ ተቋማትና በተለያዩ ባለሀብቶች አማካኝነት ቢከፈቱም ዋና መተዳደሪያ ገቢአቸው ማስታወቂያ ነውና ለነዚህ ጣቢያዎችም የተለያዩ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሰርቶ ያቀርባል፡፡
የማስታወቂያው ክፍያ እንደሬድዮ ጣቢያዎቹ እና ፕሮግራሞቹ አይነት የአየር ሽያጭ ቢለያይም ለሁሉም ጣቢያ ዋጋው የሚሰራው በሚከተለው መልኩ ነው 1. ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ የ30 ሰከንድ ወይም የ60 ሰከንድ ማስታወቂያ 2. ቅዳሜና እሁድ የ30 ሰከንድ ወይም የ60 ሰከንድ ማስታወቂያ 3. በዋዜማና በበአላት ጊዜ የ30 ሰከንድ ወይም የ60 ሰከንድ ማስታወቂያ 4. የፕሮግራም ድጋፍ (ስፖንሰርሺፕ) ማስታወቂያ ከሰኞ እስከ አርብ ለ60 ሰከንድ 5. የፕሮግራም ድጋፍ (ስፖንሰርሺፕ) ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድ ለ60 ሰከንድ 6. የፕሮግራም ድጋፍ (ስፖንሰርሺፕ) ማስታወቂያ በዋዜማና በበአላት ጊዜ ለ60 ሰከንድ
በዚህ መሰረት እንደማስታወቂያው ድግግሞሽ መጠን በፐርሰንት ቅናሽ ስለሚደረግ አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት በአካል ቢሮ መጥተው መነጋገር ይችላሉ፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የክፍያ መንገዶች የማስታወቂያውን ምርት (ቅድመ ስራ) የማያካትት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የምርት ስራው ሙሉ ለሙሉ የሚከናወነው በድርጅታችን ማዕከል ሲሆን በተቀላጠፈና ጥራት በተሞላበት ሁኔታ የታዘዝነውን ነገር ሰርተን እናቀርባለን፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|