የማስታወቂያ ስራ - የኢንተርኔት |
የኢንተርኔት ማስታወቂያ፡- ይህ የማስታወቂያ ዘርፍ ባደጉት ሀገራት ዘንድ በስፋት እየተጠቀሙበት የሚገኝ ሲሆን በእኛም አገር ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ መንግስታዊና የግል ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦችን ጨምሮ የራሳቸውን ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት አይነተኛ የማስታወቂያ ዘርፍ ነው፡፡ በመላው አለም ዙሪያ ለሃያ አራት ሰአት ያህል ማንኛውም የበይነ-መረብ ማለትም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሊገለገልበት የሚችል የማስታወቂያ አይነት ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ ድረ-ገፆች ላይ በቀላሉ ሊታይ የሚችል የማስታወቂያ ዘርፍ በመሆኑ የእኛም ድርጅት በቀጣይነት የተለያዩ ንድፎችን በመስራት የኦንላይን ግብይት በሀገራችን እስኪጀመር ድረስ በአካል ግብይት በማከናወን አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
የማስታወቂያው ክፍያ የእኛን ድረ-ገፅ ጨምሮ በሌሎች ዌብሳይቶችና ማህበራዊ ሚዲያዎች የገፅ ሽፋን ሽያጭ ቢለያይም ለሁሉም ድረ-ገፅ ዋጋው የሚሰራው በሚከተለው መልኩ ነው 1. ድረ-ገፅ ወይም አፕሊኬሽን በተከፈተ ቁጥር ቀድሞ የሚታይ ተለዋዋጭ ምስል (revolver advert) ያለው ማስታወቂያ 2. የ30 ሰከንድ ወይም የ60 ሰከንድ ቪድዮ ምስል ያለው ማስታወቂያ ድረ-ገፅ ወይም አፕሊኬሽን በተከፈተ ቁጥር የሚታይ 3. በድረ-ገፅ ራስጌ ላይ በተለያየ መጠን (ፒክስል) ተለዋዋጭ ምስል (revolver advert) ያለው ማስታወቂያ በተመረጡ ገፆች ላይ የሚቀመጥ 4. በድረ-ገፅ ጎን በኩል ላይ በተለያየ መጠን (ፒክስል) ተለዋዋጭ ምስል (revolver advert) ያለው ማስታወቂያ በተመረጡ ገፆች ላይ የሚቀመጥ 5. በድረ-ገፅ ራስጌ ላይ የሚለጠፍ የንግድ ስም፣ አርማና አድራሻ ያረፈበት ቋሚ ምስል (static advert) ያለው ማስታወቂያ በተለያየ መጠን (ፒክስል) በተመረጡ ገፆች ላይ የሚቀመጥ 6. በድረ-ገፅ ጎን በኩል የሚለጠፍ የንግድ ስም፣ አርማና አድራሻ ያረፈበት ቋሚ ምስል (static advert) ያለው ማስታወቂያ በተለያየ መጠን (ፒክስል) በተመረጡ ገፆች ላይ የሚቀመጥ 7. በድረ-ገፅ ግርጌ ላይ የሚለጠፍ የንግድ ስም፣ አርማና አድራሻ ያረፈበት ቋሚ ምስል (static advert) ያለው ማስታወቂያ በተለያየ መጠን (ፒክስል) በተመረጡ ገፆች ላይ የሚቀመጥ 8. በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ በገፃቸው መሀል ላይ በፎቶ ምስልና በፅሁፍ የሚገለፅ ማስታወቂያ ወይም ስፖንሰርሺፕ ለአንድ ሳምንት ወይም ለአንድ ወር የሚቆይ 9. በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ በገፃቸው መሀል ላይ በቪድዮና በፅሁፍ የሚገለፅ ማስታወቂያ ወይም ስፖንሰርሺፕ ለአንድ ሳምንት ወይም ለአንድ ወር የሚቆይ
በዚህ መሰረት ከተራ ቁጥር 1 - 6 ድረስ ለአንድ ወር፣ ለሶስት ወር፣ ለስድስት ወር ወይም ለአንድ አመት የሚቆዩ ማስታወቂያዎች የተለያየ ተመን ስላላቸው በአካል ቢሮ መጥተው መነጋገር ይችላሉ፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የክፍያ መንገዶች የማስታወቂያውን ምርት (ቅድመ ስራ) የማያካትት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የዲዛይን ስራው ሙሉ ለሙሉ የሚከናወነው በድርጅታችን ማዕከል ሲሆን በተቀላጠፈና ጥራት በተሞላበት ሁኔታ የታዘዝነውን ነገር ሰርተን እናቀርባለን፡፡
|
Dear this website visitors, all the web pages are established in Amharic (Ethiopian) language font so please use or install Power Geez program in your PC in order to browse it properly if strange symbols appeared on your laptop when you open it. Otherwise please use translation tools. |
"ሰናይ ዓለም " የሬድዮ ፕሮግራም
የማስታወቂያ ስራ
የግንኙነት ስራ
የቢዝነስ መድረክ
የዲጅታል ስራ
የመፅሀፍ ግምገማ
"ሲላ" አጭር የመረጃ መፅሄት
"አላማ" ሽልማት
"ሀበሻ" ቤተ-መዘክር
|
|
|
|